አ ን ኮ በ ር ወ ረ ዳ ል ማ ት
ማ ኅ በ ር
የአንኮበር ልማት ማህበር ምሥረታና ተግባራት
1. ምሥረታ
በአንኮበርና ከአንኮበር ውጪ ያሉ የአካባቢው ተወላጆችና ደጋፊዎች በሰኔ 9 1999 ጎረቤላ ላይ ባደረጉት ጠቅላላ ጉባዔ፣ 15 አባላት ያሉት ቦርድና 5 አባላት ያሉት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መርጠው ይህን የልማት ማህበር አቃቁመዋል፡፡ ጠቅላላ ጉባዔው ባመት አንዴ ሲሰበሰብ፣ ቦርዱ አራት ጊዜ ይሰበሰባል፡፡ ማህበሩም ከኅዳር 12 2000 ዓም- ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ፍትሕ መምሪያ በመዝገባ ቁጥር 47/2000 ተመዝግቦ ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶአል፡፡
ቅርንጫፍ ማህበራት
ደብረብርሃን
አዲስ አበባ
ናዝሬት
በልሎች ከተሞችና
በውጭ አገሮች ይኖሩታል፡፤
2. ለምን ተመሠረተ?
አባላት ማህበሩን የመሠረቱበት ዋና ዓላማ፣ የአንኮበር ሕዝብና ድርጅቶች፣ በልማት በኩል የሚያደርጉትን ትግል፣ አገር ውስጥና ከአገር ውጪ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች እገዛ እንዲያደርጉ ለማስተባበርና ልማትን ለማፋጠን አስተዋፅዖ ለማድረግ ነው፡፡
3. እገዛ ለምን አስፈለገ?
አንኮበር ከሌሎች ብዙ የኢትዮጵያ ክፍሎች ቀደም ብላ በዕውቀት፣ በሀብት፣ በገናናነት ትታወቅ ነበር፡፡ ከአፄ ይኩኖ አምላክ ጀምሮ የበርካታ ሕዝቦች መናኸሪያ ሆና እርሻና ከብት ርቢ ዳበሮ፣ በአሊዮ አምባ በኩል ሰፊ አገር አቁዋራጭ ንግድ ተዘርግቶ፣ አድጋ ነበር፡፡ የመንግሥቱ ሥልጣንና የንግዱ መሥመር ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ከተዛወረ በኋላ፣ አንኮበር እየተቆራቆዘች እየደኸየች መጣች፡፡ ዛሬ አንኮበር ከሌሎች የኢትዮጴያ ከፍሎች ጋር ስትወዳደር እጅግ ኋላ ቀር ናት፡፡ ምንም ዓይነት ፈብሪካ ሆነ ማዕድን የማይታይባት፣ ይባስም ብሎ ለገበያ የሚውል ይኸ ነው የሚባል የእጅ ሥራ የማይገኝባት ቦታ ናት፡፡ ከብዙ ዘመን አገልግሎት በኋላ፣ ሕዝብም እየበዛ፣ ደኑ እየተራቆተ፣ መሬቱ እየደኸየና እየጠበበ፣ የእርሻ ምርት በማሽቆልቆሉ ምክንያት፣ ድህነት ተስፋፍቶአል፡፡
የአንኮበር ሕዝብና ድርጅቶች ከዚህ ድህነት ለመላቀቅ ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በየቦታዉ ያሉ የአንኮበር ተወላጆች፣ ለዚህ ትግል ከጎኑ እንዲሠለፉ፣ እገዛ እንዲያደርጉ፣ ሕዝቡና ድርጅቶቹ ይመኛሉ፣ ይጠብቃሉ፡፡ጥሪም አቀርበዋል፡፡ ሀብት ያላቸው፣ ወደ አካባቢው መጥተው ሥራ እንዲከፍቱ፣ ሌሎችም በዕውቀታቸውና በገንዘብ እንዲረዱ ሕዝቡ ይማጸናል፡፡
4. ማኅበሩ በምን መስኮች ላይ እገዛ ያደርጋል?
የወረዳው ባለሙያዎችና ምሁራን በማህበሩ ዙሪያ ተሰባስበው ባካሄዱት ውይይት፣ መደገፍ ይገባቸዋል የሚባሉትን የልማት ተግባራት አሰባስበዋል፡፡ የአንኮበር ልማት ማህበር ቦርድም በበኩሉ ይህን ጥናት መርምሮ፣ እንደሚከተለው ወስኖአል፡፡
በገበሬ ቤተሰብ ደረጃ፣በመንደር፣ በቀበሌ እንዲሁም በወረዳ ደረጃ ታች የተዘረዘሩትን የልማት ተግበራት፣ የአንኮበር ተወላጆች በዕውቀት፣ በቆሳሰቁስና በገንዘብ ድጋፍ እንዲሰጡ፣ ልማት እንዲፋጠን የማህበሩ አባላት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዲያደረጉ፣ ቦርዱ ጥሪ ያቀርባል፡፡
5. በገበሬ ቤተሰብ ደረጃ የሚደገፉ የልማት አውታሮች
የወረዳው መሬት አቀማመጥ እጅግ ኮብታማና ተራራማ ሆኖ፣ 8 በመቶ ያህል ብቻ ሜዳማ ነው፡፡ በደን ከመራቆቱ የተነሳ፣ ገበሬው በእርከን ቢከላከልም፣ መሬቱ እየታጠበ ምርታማነቱ ቀንሶአል፡፡ ያሉት አራት ትላልቅ ጅረቶች 37 በመቶ ያህል ብቻ ለመስኖ ውለዋል፡፡ አንድ የገበሬ ቤተሰብ 0.76 ሔክታር መሬት ብቻ ያርሳል፡፡ ከወረዳው ሕዝብ 94 በመቶ የሚሆነው፣ ማለት 95 000 ሕዝብ ገበሬ ነው፡፡ የቤተሰቡም ብዛት 20 000 ያህል ይሆናል፡፡ ቤተሰቡን መግቦ ተረፈ ምረት እንደማያገኝ ይህ አኀዝ ይጠቁማል፡፡ የሕዝቡም ቁጥር እጅግ እየጨመረ መጥቶ አንድ የገበሬ ቤተሰብ ልጆቹን የሚያሰማራበት ቦታ ስለሌለው የሥራ አጥ ወጣት በዝቶአል፡፡ ስለሆነም፣ ማህበሩ ያቀደው ስልት፣ እንደሚከተለው ነው፡፡
ሀ፣ የገበሬዎችና የመሬታቸው ምርታማነት ከፍ እንዲል፣
ለ፣ ተጓዳኝ ገቢ ማስገኛ ዘዴዎችእንዲስፋፉ እርምጃ ይወስዳል፣
ሐ፣ የገበሬዎችንና ረዳት ድርጅቶቻቸው የሚያደረጉትን የልማት ጥረት ተከታትሎ ገምግሞና አወዳድሮ በገንዘብ፣ በዕውቀትና በቁሳቁስ ይደግፋል፡፡
5.1 ደን ልማትን መደገፍ የአካባቢው ወጣት በቡድን እየተደራጀ የደን ቦታእንዲሰጠውና እንዲያለማ የወረዳው አመራር ዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ፣ የፐሮጀክቱን ጥንካሬ መርምሮ ማህበሩ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
5.2 የገበሬውን ተጓዳኝ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ፣ ኮረብታማ ቦታዎችን ሸንተረሮችን፣ እንደአየሩ ንብረት፣ በፍራፍሬ ዛፎች መሸፈን፣ በተለይም ፖም፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ካዝሚር፣ ፐሩኝ፣ ፓፓያ፣ ወይን ተክልና ቡና እንዲስፋፉ ገበሬውን ያበረታታል፣ ይደግፋል ፡፡ ፖም ተሞክሮ ውጤታማ ሆኖአል፡፡
5.3 የጓሮ አትክልት እንዲስፋፋ ያበረታታል፡፡ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
5.4 የእንስሳት ዝርያን የማሻሻል ፕሮጀክት፣ ለምሳሌ የበግን ዝርያ መደገፍ፡፡
5.5 የሐር ትል እርሻ፣ መሽሩም እንጉዳይ፣ ዓሣ እርባታ፣ ጥርኝ ማርባት የመሰሉ በአነስተኛ ቦታ ላይ ሊለሙ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን እንዲጀመሩ ያነሳሳል፡፡ ይደግፋል፡
5.6 የከብት ማድለብ ፐሮጀክት ያበረታታል፣ ይደግፋል፡፡
5.7 የንብ እርባታ ፕሮጀክት ይደግፋል፣ ያሰፋፋል፡፡
5.8 ዘመናዊ የዶሮ እርባታን ያስፋፋል፡፡
5.9 እጅ ሥራን ሆነ ዕደጥበባትን በግልም ሆነ ተደራጅተው ለሚሠሩ፣ ሴቶችና ወጣቶች ፐሮጀክታቸውን ገምግሞ አወዳድሮ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
6. በመንደር ደረጃ የሚደገፉ የልማት አውታሮች
6.1 በመንደር ደረጃ ወንዞችን ሆነ የዝናብ ውሃን ተጠቅሞ በመስኖ የማልማት ፕሮጀክትን ያደፋፍራል፣ ይደግፋል፡፡
6.2 የዶሮ ሠርቶ ማሳያ ፐሮጀክት በመንደር ደረጃ ይደግፋል፡፡ የተሻለ የዶሮ ዝርያ ያቀርባል፡፡
6.3 ጥሩ የእንስሳ ዝርያ በማደል ሞዴል ገበሬን መርጦ ይደግፋል፡፡
6.4 የንብ ማነቢያ ቁሳቁሶች በመንደር ደረጃ ያቀርባል፡፡
6.5 ለእንስሳት የውሃ ገንዳ በመንደር ደረጃ እንዲሠራ ያበረታታል፣ ይደግፋል፤፤
6.6 በመንደር ደረጃ ምንጭ እንዲጎለበት ያደርጋል፡፡
6.7 ደካማና አረጋውያን በመያድ፤በዕድሮች አማካኝነት እንዲረዱ ያደርጋል፡፡
6.8 በመንደር ወንዝ በመገደብ ወይም ኩሬ በመሥራት የዓሣ ዕርባታን ስፋፋል፡፡ የዓሣ ጫጩት ያቀርባል፡፡
6.9 አትክልትና ፍራፍሬ ዘር በማባዛት ገበሬዎች እንዲያመርቱ ይረዳል፡፡
6.10 በቆላው አካባቢ የሐር ትል ምርት እንዲጀመር ጥረት ያደርጋል፡፡
7. በቀበሌ ደረጃ የሚደገፉ የልማት አውታሮች
7.1 የንብ እርባታን ለማፋጠን ከፍተኛ የሆነውን የማንቢያ ቁሳቁሶች ለምሳል፤የሰም ማተሚያ እጠረትን ለመቅረፍ፣ ዘመናዊ ሰም ማተሚያ መሣሪያ ማጣሪያ፡ ጭስ ማጨሻ በቀበሌ ደረጃ ያስተክላል፡፡
7.2<span style="font-weight: normal; font-style: normal;